Presentation is loading. Please wait.

Presentation is loading. Please wait.

መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

Similar presentations


Presentation on theme: "መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።"— Presentation transcript:

1 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

2 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? ከላይ እንደተገለጠው እግዚአብሔር የፍጥረታት ፈጣሪ መሆኑን፥ መኖሩንም፥ መለኮታዊ ባህሪይዉንና የዘላለም ሃሳቡን ለሰው ልጅ ለማሳወቅ እንደተፃፈ እንመለከታለ። በዚህም እምነት፥ ተስፋ፥ ሃሴት፥ የልብም ደስታ፥ መፅናናት፥ ተግሣፅም፥ የጽድቅ ምክርም፥ ትምህርትም እንዲሆንልን እንደተፃፈ እንገነዘባለን። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

3 [ሮሜ1017] “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”...እምነት እንዲሆነን!
መሰረታዊ ጥቅሶች [ሮሜ1017] “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”...እምነት እንዲሆነን! [ሮሜ154]“በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።”...መጽናናት እንዲሆነን! [2ጢሞ316] “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”...ለትምህርታችን፥ ለተግሳጻችንም፥ ልባችንንም ማቅኛ እንዲሆነን! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

4 መሰረታዊ ጥቅሶች [1ቆሮ1011] “ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።”....ሊገስጸን! [ኤር1516] “ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።”...ሐሤትና የልብ ደስታ እንዲሆነን! [ኤፌ617] “የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።”...መንፈሳዊ ትጥቅ እንዲሆነን! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

5 መጽሓፍ ቅዱስ... እምነት እንዲሆነን ተጽፏል፤... በዚህም የሚያድን እምነት ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!!
መጽናናት እንዲሆነን ተጽፏል፤... በዚህም አማናዊ መጽናናት ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!! ለትምህርታችን፥ ለተግሳጻችንም፥ ልባችንንም ማቅኛ እንዲሆነን ተጽፏል ፤... በዚህም ትምህርታችን ፥ ተግሳጻችንም ፥ ልብ ማቅኛችንም ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

6 መጽሓፍ ቅዱስ... ሊገስጸን ተጽፏል፤... በዚህም እዉነተኛ ተግሳጽ ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!!
ሊገስጸን ተጽፏል፤... በዚህም እዉነተኛ ተግሳጽ ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!! ሐሤትና የልብ ደስታ እንዲሆነን ተጽፏል፤... በዚህም እዉነተኛ ሐሤትና የልብ ደስታ ከርሱ ዉጭ አይመጣም!!! መንፈሳዊ ትጥቅ እንዲሆነን ተጽፏል ፤... በዚህም ያለዚህ ሴይፍ በሴይጣን ለይ ድል ፈጽሞ አይታሰብም!!! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

7 በዚህም የተነሳ በግልም ይሁን በጋራ ከሚደረግ ዘወትራዊ የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናት ዉጭ ፤ ክርስቲያናዊ ሕይወትን መኖርም ይሁን እግዚአብሔርን ማወቅ አንደማይቻል እንገነዘባለን። “It is impossible to live Christian life and know God without knowing the word of God.” [Dr. W.E.Bell] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

8 ከላይ ባየናቸዉ መሰረታዊ ጥቅሶች፡- “I believe in the bible from cover to cover but I don’t know what is within cover to cover.” [Someone] የሚለዉ አካሔድ የሚያዋጣ አይደለም። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

9 [መዝ11989] “አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።”
....ቃሉ ዘላለማዊ፥ የእግዚአብሔር፥ በሰማይም የሚኖር ነዉ! [መዝ1830] “የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።” .....ቃሉ የነጠረ፥ ለሚታመኑበትም ጋሻ ነዉ! [መዝ334] “የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።” .....ቃሉ ቅን ነዉ! [ምሳ305] “የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።” .....ቃሉ የተፈተነ ነዉ! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

10 [ዩሃ153] “እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ”
.....ቃሉ ያነጻል፤ መንጻት ከቃሉ ዉጭ የለም! [1ጴጥ123-24] “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።” ......ቃሉ የማይጠፋ ዘላለማዊ ነዉ! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

11 ማስገንዘቢያ... እስካሁን እንዳየነው ፍጥረታቱም ፥ መጽሓፍ ቅዱስም “ነገር ሁሉ ከእርሱ ፤ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ” አንድ ጌታ እግዚአብሔር እንዳለ እንደሚናገሩ ነው። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

12 መጽሓፍ ቅዱስ ያልደረሳቸው ፤ ጌታም ያልተሰበከላቸው ዕጣቸው ምንድር ነው
መጽሓፍ ቅዱስ ያልደረሳቸው ፤ ጌታም ያልተሰበከላቸው ዕጣቸው ምንድር ነው? መጽሓፍ ደርሷቸው ጌታም ተሰብኮላቸው ካላመኑት ጋር ቅጣታቸው እኩል ነውን? መልስ፡ ይህን እርሱ ብቻ ያውቃል! “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” ይላልና! [ሮሜ834] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

13 ሀ.በዚህም.... ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነና ፥ ፍርዱም ትክክል ፣ ዙፋኑም የዘላለም እንደሆነ ካመንን፤ ይኸዉ ጌታ ስለ ሰው ዘር ሁሉ ፥ስለ በደላቸዉም አልፎ እንደተሰጠ ፥ እነርሱንም ለማጽደቅ እንደተነሳ፥ በግርማው ቀኝ ሆኖም ዘወትር እንደሚያማልድ ካመንን፤ እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና ፤ ከእኛ ይልቅም እርሱ ግድ ስለሚለው ፥ እስከሞት በወደደው ፍቅሩ እና በቅን ፍርዱ ይፈርድላቸዋል። ለሰው ፊት ያደላ ዘንድ እግዚአብሔር ሰዉ አይደለምና። [መዝ456-7፥14517 ፤ ሮሜ211፥425፥58-10፥834፥9 14፣22፥1129፥ ] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

14 በአብርሃም ቤት የነበሩት ሁሉ ፤ ከርሱ በየዕለቱ በተማሩት አምነዉ መገረዛቸው ፤ ግዝረት የማመን ምልክት ነዉና!
ለ.አንድም... በሀ የተገለጠዉን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በመጽሓፍ ቅዱስ የተንጸባረቁ እውነታዎችን በጥንቃቄ ስናጠናቸዉ፥ (ምናልባት) እግዚአብሔር፥ መኖሩን በፍጥረቱ በኩል የተረዳውን [ሮሜ117] ፤ ወደ መጽሓፍ ቅዱስ ዕውቀት የሚመራዉ፤ በመጽሓፍ ቅዱስ የተገለጠዉን ብርሃን የተቀበለዉን ደግሞ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት የሚመራዉ ይመስላል። ለማስረጃ ያህል፦ በአብርሃም ቤት የነበሩት ሁሉ ፤ ከርሱ በየዕለቱ በተማሩት አምነዉ መገረዛቸው ፤ ግዝረት የማመን ምልክት ነዉና! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

15 በብሉይ ኪዳን በእስራኤል አምላክ ያመኑ አህዛብ ሁሉ፤ ተገርዘዉ እግዚአብሔርን ያመልኩ ፥ መስዋዕትም ያቀርቡ፥ እንደዉም በቤተመቅደስ ዉስጥ “የአህዛብ አደባባይ” ተብሎ የተለየ ቦታ ተሰጥቷቸው እንደነበረ እናያለን። ተስፋ ያልተገባላቸዉ ቢሆኑም፤ በሥነ ፍጥረት የተረዱት ፈጣሪ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደሆነ አዉቀዉ አምነዉበታልና! እንደውም አምላክሽ አምላኬ ፥ ሕዝብሽም ሕዝቤ ይሆናል፤ በምትሞችበት እሞታለሁ ፥ በምትቀበሪበትም በዚያ እቀበራለሁ የሚል አስደናቂ እምነት የነበራትን ሞአባዊቱን ሩት፤ ጌታ በፈቃዱ የራሱ ትውልድ ሀረግ ሲያደርጋት እንመለከታለን። [ሩት14፥16-17] ሞአባዊያን እስከ አስር ትውልድ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ እንዳይገቡ የከለከላቸው መሆናቸዉን ልብ ይሏል።[ዘዳ233-6 ዘኁ22-24] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

16 የነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስን የትንቢት መጽሓፍ እያነበበ፥ ከኢየሩሳሌም ስግደት መልስ ላይ የነበረው ጃንደረባ ወደ ክርስቶስ ዕውቀት ሲመጣ እናያለን። [ስራ826-40] እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያመልክ፥ ለሕዝብም እጅግ ምፅዋትን ያደርግ የነበረው ቆርኖሌዎስም ወደ ዘላለም ሕይወት መንገድ መጠራቱን እንመለከታለም። [ስራ10] ጃንደረባዉም ይሁን ቆርኖሌዎስ የአይሁድ እምነት ተከታዮች እንጂ በሥጋ የአብርሃም ልጆች እንዳልነበሩ እንመለከታለንና! በወገኑ የእስክንድርያ አይሁዳዊ ሰው የሆነዉ አጵሎስ በጵርስቅላና አቂላ በኩል የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ተገልጦለታል። [ስራ ] እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ፥ የጌታን መንገድ የተማረ ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበርና።  ገማልያልን ልብ ይሏል! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

17 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? ማጠቃለያ
መጽሓፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እርሱ የዘላለም አምላክ “ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ” እንደሆነ ሊያሳውቀን እንደተጻፈ እንገነዘባለን። [ኤር5115] መጽሓፍ ቅዱስ ለእምነታችን፥ ለተግሳጻችን፥ለመጽናናታችን፥ በጽድቅ ላለው ምክርም ሁሉ ይሆነን ዘንድ ለትምህርታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን መጽሓፍ እንደሆነ እንገነዘባለን። መጽሓፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንድናውቀው የተጻፈልን መጽሓፍ በመሆኑ ኦሪጅናል ኮፒዉ ለይ ስህተት የሌለበት inherent እንደሆነ ይገባናል። ስለዚህም ማንም እንደወደደ ሊተረጎመው የማይችለው መጽሓፍ እንደሆነ እንገነዘባለን። [2ጴጥ120-21] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

18 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? ማጠቃለያ
ያለ እግዚአብሔር ቃል ዕዉቀት ክርስቲያናዊ ሕይወትን መኖርም ይሁን እግዚአብሔን ማወቅ ፈጽሞ አይቻልም። [ሮሜ128] “እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው” “እግዚአብሔርን ለማወቅ በወደዱት መጠን እግዚአብሔር የሚገባውን ያደርጉ ዘንድ ለሚረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው” ክርስቲያናዊ ሕይወትን መኖር የምንችለዉ መለኪያ እግዚአብሔን ለማወቅ በምንወደዉ መጠን ብቻ ይወሰናል! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

19 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? ማጠቃለያ
እግዚአብሔር ማወቅ ከመስዋዕቶች ሁሉ ይበልጣል! “ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና።” [ሆሴ66] እግዚአብሔር ማወቅ በራሱ የዘላለም ሕይወት ነዉ! “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” [ዩሃ173] እግዚአብሔር ካለማወቅ ሕዝብ ይጠፋል! “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።” [ሆሴ46] ምሳሌ፡ 2ነገ22 መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

20 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? ማጠቃለያ
እግዚአብሔር ማወቅ ሥራን ያቀናል! “ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ሥራቸውን አላቀኑም የግልሙትና መንፈስ በውስጣቸው አለና እግዚአብሔርንም አላውቁምና።” [ሆሴ54] እግዚአብሔር እርሱን ለማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ተዘጋጅቶ ይጠብቃ! “እንወቅ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል።” [ሆሴ63] እግዚአብሔር ማወቅ በራሱ የማይቀሙት ዕድል ነዉ! “ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” [ሉቃ1042] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

21 መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

22 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ይህ መጽሐፍ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ተጽፏል! [2ጢሞ316-17] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

23 1ኛ. ሁሌም ለማወቅ መቅረብ፤ ቃሉንም ለማጥናት ቅድሚያ መስጠት ይገባል።
እንግዲህ.... እግዚአብሔርን ባወቅነዉ መጠን ብቻ መጽናትና መጽናናት ያለበትን የጽድቅ ሕይወት የምንኖር ከሆነ፡ 1ኛ. ሁሌም ለማወቅ መቅረብ፤ ቃሉንም ለማጥናት ቅድሚያ መስጠት ይገባል። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

24 እግዚአብሔርን ባወቅነዉ መጠን ብቻ መጽናትና መጽናናት ያለበትን የጽድቅ ሕይወት የምንኖር ከሆነ፡
እንግዲህ.... እግዚአብሔርን ባወቅነዉ መጠን ብቻ መጽናትና መጽናናት ያለበትን የጽድቅ ሕይወት የምንኖር ከሆነ፡ 2ኛ. ሁሌም ለመማር በተዘጋጀ ልብ መቅረብ፤ እግዚአብሔር የሚያስተምሩትን ሳይሆን ከርሱ ለሚማሩት ሚስጢሩን ይገልጻልና! ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸዉ ተምረዋል። [ማር931፥ዩሃ14-17] ለደቀ መዛሙርቱ ብቻቸዉ ምሳሌዉን ተርጉሞላቸዋል። ለደቀ መዛሙርቱ አእምሮአቸዉን ከፍቶላቸዋል። [ሉቃ2445] ደቀ መዛሙርቱን እስካረገበት ቀን ድረስ አስተምሯቸዋል። [ሥራ11] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

25 እግዚአብሔርን አዉቀን አንጨርሰዉም! እግዚአብሔር ሁሌም አዲስ ዕዉቀት አለዉ።ቀድሞ ባወቅነዉ ዕዉቀት ዛሬ አናዉቀዉም። ስለርሱ ብናነብም፥ ብንሰበክም፥ ብንሰብክም፤ እግዚአብሔርን ተምረን አንጨርሰዉም። ሁሌም በፊቱ ዕዉቀታችን ጎደሎ ነው። [ዩሃ31-22] ከዕዉቀት አሁን ከፍለን ብቻ እናዉቃለንና! [1ቆሮ1312] “እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው።” [1ቆሮ81-3] መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

26 ማስገንዘቢያ ምን አልባት እገሌ ከእገሌ ትንሽ የተሻለ ሊያዉቅ ይችላል፤ የዕዉቀት መስፈሪያ በሆነዉ በእግዚአብሔር ፊት ግን ደንቆሮ ነዉ። “ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅምና።” [1ቆሮ211] በዚህም “ዛሬ እንኳ የምንማረዉ ሁሌም የምናዉቀዉን ክፍል ነዉ።.... ” የሚለዉ የተለመደዉ የሰባኪያኑ አባባል በመሰረተ ሃሳቡ ፍጹም የተሳሳተ እንደሆና እንመለከታለን። የመጽሓፍ ቅዱስ አስተምሮ ሁሌም እንደ ሂሳብ ትምህርት 1+1=2 አይደለም። ኤልያስ መጥምቁ ዩሃንስ ሊሆን ይችላልና! መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

27 በዚህም የተነሳ.....[ምሳሌ] በዚህም የተነሳ መጽሓፍ ቅዱስን ስናነብም ይሁን ስንማር ቀድሞ ያወቅነዉን ዕዉቀት አስቀምጠን፤ ልክ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚማር፥ እንደሚሰማም ሆነን በመቅረብ ተምረነዉ፤ የቤሪያ ሰዎች እንዳደረጉት ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር በማስተያየት የተሳሳትነዉን ማረም፥ ያላወቅነዉን ማስቀረት፥ ያወቅነዉን ማጠናከር፥ ልባችን ያላረፈበትን ደግሞ መያዝና መጸለይ ይገባል እንላለን። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።

28 በዚሁ መንፈስ “አሮጌዉ በር ወይም የመጀመሪያዉ መጀመሪያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉን፥ መሰረታዊዉን በሰዉ ልጅ ለይ ያለዉን የእግዚአብሔር አጀንዳ ከዘፍ1-3 ባሉት ምዕራፎች ለይ በመመስረት የሚያብራራዉን ትምህርት፣ በመሰሉን ዋና ሃሳቦች ለይ በመመርኮዝ እናቀርባለንና ሚስጢር ገላጩ ጌታ ሚስጢሩን ይግለጥልን። መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።


Download ppt "መጽሓፍ ቅዱስ ለምን ተጻፈልን? መሰረታዊ አስተምሮዉን ባልቀየረ መልኩ ይህንን ትምህርት በማንኛዉም ዓይነት መንገድ ለሌላዉ በማዳረስ በአገልግሎቱ ይሳተፉ።"

Similar presentations


Ads by Google